የማህበራችን የቦርድ አባል እና የቪክትሪ ኮሌጅ ፕሬዚደንት የነበሩት ዶ/ር አያናው አድማሱ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ግንቦት 28/2016 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። የቀብር ስነ-ስርዐታቸው ነገ ግንቦት 29/2016 ጉርድ ሾላ በሚገኘው ሰዓሊተ ምሕረት ቤተ-ክርስትያን ከቀኑ 6:00 ይከናወናል።

ማህበራችንም በዶ/ር አያናው አድማሱ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል።