
የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና
ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ማኀበር
“የተሸሻለ መተዳደሪያ ደንብ”
መግቢያ
የኢትዮጵያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንቦታ ለማፋጠን ትምህርት የሚጫወተው ሚና ወሳኝ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የሀገሪቱ የትምህርት እና የኢነቨስትመንት ፖሊሲ በፈጠረው ዕድል በመጠቀም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በከፍተኛ ፍጥነት ያደጉ ሲሆን በዘርፉ ነባር ዕድሜ ባላቸው ተቋማት አነሳሽነት በማኅበር የመደራጀት እና ዘርፉን አስተባብሮ የመምራት አስፈላጊነት በመታመኑ በ1995 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ጥላ ስር በመደራጀት ጥቂት ተቋማት የጋራ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ይህንን በአዲስ አበባ ብቻ የተገደበ እንቅስቃሴና አደረጃጀት በመላው ሀገሪቷ ለማስፋፋት ፍላጎቱ የነበረ ቢሆንም ብዙዎቹ ተቋማት የትርፍ በማህበራት አደረጃጀት ስለነበራቸው የጋራ ማህበሩን ለማስመዝገብ የተደረገው ጥረት ብዙዎቹ ተቋማት የትርፍ በማህበራት አደረጃጀት ስለነበራቸው የጋራ ማህበሩን ለማስመዝገብ የተደረገው ጥረት በፍትሕ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በኩል ለተወሰኑ ጊዜያት ተቀባይት ሣያገኝ ቆይቷል፡፡ ሆኖም በውቅቱ የነበሩት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች የማህበሩን መመስረት አስፈላጊነት ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር ባደረጉት ምክክር ማህበሩ በ12 (አስራ ሁለት) መሥራች ተቋማት ሚያዚያ 22 ቀን 1996 ዓ.ም. በሕጋዊነት ለሚሠረት ችሏል፡፡
በወቅቱ የነበረው የመተዳደሪያ ደንብ መሻሻል ባስፈለገባቸው ጊዜያቶች ማለትም በ1998፣ ዓ.ም. በነሃሴ 1999፣ በጥር 2001፣ እና በ2005 እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡
Please Open the Following PDF file for Detailed Information…..


