የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች በተፈጠረው የፀጥታ ትምህረታቸውን ማቋረጣቸው ይታወቃል፡፡
ስለሆነም የተቋረጠውን ትምህርታቸው በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ባሉ የግል ትምህርት ተቋማት መቀጠል ችችሉ ዘንድ አዲስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በደብዳቤው ላይ የተገለፁና ሌሎች ተጨማሪ አስፈላጊ መረጃዎች መሟላታቸውን አረጋግጠው ተቀብለው ማስተማር እንዲችሉ የተፈቀደ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለተጨማሪ ማብራርያ አባሪ የተደረገውን ደብዳቤ ይመልከቱ፡፡