ጉዳዩ፡- 2015 ዓ.ም የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ እጩ ሰልጣኞች ስም ዝርዝር እንዲላክልን  ሰለማሳሰብ፤

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማሕበር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን አቅም የማጎልበት  ስራ በየዓመቱ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ለ2015 በጀት ዓመት ትምህርት ሚኒስቴር ለእያንዳንዱ የማሕበሩ አባል ተቋማት በሰጠው የእጩ ሰልጣኖች ብዛት (ኮታ) ማለትም፡-

  • ለዩኒቨርሲቲዎች፡- 02 ሰው ለ3ኛ ዲግሪ እና 02 ሰው ለ2ኛ ዲግሪ
  • ለዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች፡- 01 ሰው ለ3ኛ ዲግሪ እና 01 ሰው ለ2ኛ ዲግሪ
  • ለኮሌጆች፡– 01 ሰው ለ2ኛ ዲግሪ ብቻ

ተቀብሎ ለማስተማር የተፈቀደልን ስለሆነ ተቋማት ከላይ በተጠቀሰው የእጩ መምህራን ቁጥር መሰረት በማድረግ በተቋማችሁ የሚገኙትን መምህራን በራሳችሁ መስፈርት መሰረት በመመልመል ከስር በተያያዘው ፎርም ተለይቶና ተሞልቶ እሰከ ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ድረስ በተቋሙ የበላይ ሐላፊ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ስካን በማድረግ በሚከተለው የኢሜል አድራሻ  (tegegnealemie12@gmail.com) ወይም በአካል በመቅረብ ገቢ እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡