በኮርያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተሾሙ።
አምባሳደር ሽፈራው በቀድሞ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በኦዲትና አቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊነት፤ በምክትል ርእሰ መስተዳደርነት እና ለሰባት ዓመታት ክልሉን በርእሰ መስተዳደርነት መርተዋል፡፡በተጨማሪም የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር፤ የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና በኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡
(ምንጭ:-የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን)